What We Believe
Our statement of faith outlines the core biblical truths that guide our worship, ministry, and collective lives.
The Authority of the Bible
ስድሳ ስድቱን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋሳ ቃል፣ ምንም ስህተት የማይገኝበት ፣ እምነትን እና ተግባርን በሚመለከት ሁሉ የመጨረሻው ሥልጣን ያለው ፣ህያው እና ዛሬም የሚሰራ ፣ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡
The Holy Trinity
በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ አንድ አምላክ ፣እናምናለን፡፡
The Sovereignty of God
በመፍጠር ስራ፣ ፍጥረትን በመጠበቅ ፣ በመገለጥ ፣በመዋጀት እና በመጨረሻው ፍርድ የእግዚአብሔርን ፍፁም ሥልጣን እና የበላይነት እናምናለን፡፡
Jesus Christ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ የተላከ መሆኑን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መፀነሱን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፣ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ፣ ለሰው ልጃች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን ፣ መቀበሩን፣ በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን፣ ወደ አብ ማረጉን እና አሁንም በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ እንደሚማልድ ፣ ደግሞም በህያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በክብርና በግርማ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡
The Holy Spirit
መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ባሕርያት ሁሉ ያሉት ፍጹም አምላክ እንደሆነ እና አምልኮ እና ስግደት እንድሚገባው እናምናለን፡፡
The Fall of Man
ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ በኃጥያት መውደቁን እና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡
Salvation by Grace
ሰው ከኃጢአት ዕዳ ፣ ኃይልና ቅጣት ፣ ሊድን የሚችለው ኃጥያት የለለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ስራ ብቻ በመሆኑ ኃጥያተኛ በእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚጽድቅ እናምናል፡፡
Regeneration
ኃጥያተኛ በኃጥያቱ ተፀጽቶ ንሰሐ እንዲገባ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ እንሚሰራ እናምናልን፡፡
Baptism in the Holy Spirit
መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ፣ አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ኃይልን እንደሚቀበልና በልሳን እንደምናገር በየጊዜውም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን፡፡
Spiritual Gifts & Miracles
መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ለአማኞች ልዩ ልዩ የጸጋ ስጦታዎችን በማካፈል፣ድውዮችን በመፈወስ ፣ አጋንትን በማውጣትና ፣እና ተዐምራትን በማድረግ እንመድሰራ እናምናለን፡፡
The Mission of the Church
ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሰጣትን የታላቁን ተልዕኮ አደራ በመወጣት ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ እንድትሰብክ እና አማኞች ደቀ መዛሙርት በማድረግ ለክርስቶስ አካል መታነጽ አስፈላጊውን ሁሉ መፈጸም እንደምትችል መንፈስ ቅዱስም ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌል ሰባኪዎችን ፣እረኞችን እና አስተማሪዎችን እንዲሁም ሌሎች የአገልግሎት ስጦታዎችን እንደሚሰጥ እናምናለን፡፡
One Holy Church
ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም የተወለዱ ሁሉ በሚገኙባት፣ የክርስቶስ አካል በሆነች፣ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡
Baptism & The Lord's Supper
ጌታችን እና መድኅንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰረት ፣ዳግም የተወለደ አማኝ ከክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ጋር መተባበሩን እንዲሁም ለኃጥያት መሞቱን እና ለጽድቅ መነሳቱን ለመግለጽ በአብ, በወልድ, እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ በመጥለቅ እንዲጠመቅ እንዲሁም ጌታ ዳግም እስኪመጣ ሞቱን ለመናገርና , ከጌታ እና ለአማኞች ጋር ያለውን ኅብረት ለመግለጽ የጌታ እራት እንደሚካፈል እናምናለን፡፡
Eternal Life & Judgment
በሙታን ትንሳኤ፣ በኃጥያተኞች ላይ በሚደርሰው የዘላለም ፍርድና አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ህይወት እናምናለን፡፡
Questions of Faith?
Our pastoral team is available to walk through any questions about our statement of faith.
Contact Pastoral Team